Elias Girma

የቤተክርስቲያን አባላት ማደራጃ ሲስተም

ይህ ሲስተም ቤተክርስቲያናት የአባላቶቻቸውን መረጃ በተደራጀ እና ወጥነት ባለው መልኩ እንዲይዙና አባሎቶቻቸውን መረጃ በሚገባ መልኩ በመያዝ መከታተል እንዲችሉ ለማገዝ የተሰራ ሲስተም ሲሆነ በዋናነት አራት ተግባራትን ለመከወን ያስችላል። ሲስተሙን የማበልፀግ ስራ ቀጣይነት ያለው ሲሆነ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የአባላት የክፍያ ሁኔታ፣ የቤተክርሰቲያን አስተዳደራዊ ጉዳዮች፣ የቤተክርስቲያን ወጪና ገቢ እንዲሁም የአባላት የመማማሪያ መንገድ የሚካተትበት ይሆናል።
ሙሉ መረጃውን በዚህ ሊንክ ዳውንሎድ ያድርጉ።

  • የአባላት መረጃ ማደራጀት
    • አዲስ አባል መመዝገብ
    • የአባላት መረጃ ማስተካከል
    • የአባላት የዝውውር መረጃዎች
    • የአባላት የጉብኝት መረጃዎች
    • የአባልነት ሰረተፍኬት ማዘጋጀት
    • የአባላት አስራት ክፍያ መከታተያ
  • የአባላት የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት/የቤት ህብረት መረጃ ማደራጃ
    • አዲስ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት/የቤት ህብረት ቡድኖችን መመስረት
    • አባላትን በየመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት/በየቤት ህብረቱ መመደብ
    • የአባላት የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት/የቤት ህብረት ስርጭትን መከታተል
    • በመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት/የቤት ህብረት ውስጥ የታቀፉ እና ያልታቀፉ አባላት ዝርዝር መመልከት
  • የአባላት የአገልግሎት ዘርፍ መረጃ ማደራጃ
    • አዲስ የአገልግሎት ዘርፎችን ማስጀመር
    • አባላትን ወደየአገልግሎት ዘርፎች ምድባ መስራት
    • በአገልግሎት ዘርፎች ውስጥ የታቀፉ እና ያልታቀፉ አባላት ዝርዝር መመልከት
    • በተለያዩ ወቅቶች ያገለገሉ የአባላት ዝርዝር በቀላሉ ማግየት
  • ልዩ ልዩ ሪፖርቶች
    • ዝርዝር እና ወቅታዊ የአባላት ሪፖርት
    • የአገልጋዩች የጉብኝት ሪፖርቶች
    • የአባላት ግለታሪኮች(ግላዊ መረጃ፣ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት/የቤት ህብረት መረጃና የአገልግሎት ታሪክ መረጃ)
    • የአባላት የመኖርያ አካባቢ ስርጭት
    • ወቅታዊ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት/የቤት ህብረት ምድቦች እና የአገልግሎት ዘርፎች ሁኔታ ሪፖርት
    • ሌሎችም